top of page

ሳምታዊ የጤና ትምህርት/Weekly Health Education Post for Community-አምስተያ ሳምንት

Title/ርህስ-Multi Drug Resistant Tuberculosis/TB-የሳንባ ነቀርሳ

ተላላፊ የሳንባ ነቀርሳ ላለባቸው በሽተኞች እቤት ውስጥ የሚደረግ የመተንፈሻ
ጥንቃቄዎች 

የራስዎን የቲቢ ተውሳክ ወደ ሌሎች ሰዎች እንዳይተላለፍ ለመከላከል ማድረግ ያለብዎት በጣም ጠቃሚ ነገሮች እናሆ፤
      በሚያስልዎ ወይም በሚያስነጥስዎ ጊዜ ሁል ጊዜ አፍዎንና አፍንጫዎን ይሸፍኑ። አንዳንድ ሰዎች ሙቅ ፈሳሾችን በሚጠጡበት ጊዜ በትንሹ
ይስላሉ።
 እቤት እያሉ፣ እንደ ሽንት ቤት ወይም ኩሽና በመሳሰሉ ሌሎች ሰዎች በሚጠቀሙ ክፍሎች ለአጭር ጊዜ ብቻ ይቆዩ። እቤት ውስጥ ከርስዎ
ጋር ከሚኖሩ የቤተሰብ አባላት ጋር አብረው ሲኖሩ ጭምብል ማድረግ አያስፈልግዎትም።
 ከጤና አጠባበቅ ሠራተኞች በቀር ጎብኚዎች ወደ ቤትዎ እንዲመጡ አይፍቀዱ። ሌሎች ሰዎችን ለመጎብኘት አይሂዱ።
 ከቻሉ፣ እቤትዎ እያሉ፣የአየር ማረገቢያ ወይም መስኮቶችን ይክፈቱ። ይህም አየር በአካባቢው እንዲዘዋወር ይረዳል። እርስዎ ከቤትዎ ውጭ
በክፍት ሥፍራ ያለ ጭምብል መሄድ ይችላሉ።
 በቀጥታ የሚታይ ህክምና ((Directly Observed Therapy (DOT)) TBዎን ለማዳን ምርጥ ዘዴ ነው። ሀኪምዎና የህዝብ ጤና ጥበቃ
ነርስ ስለ DOT በተመለከተ ይነግሩዎታል። የህዝብ ጤና አጠባበቅ ሠራተኛ የTB መድኃኒትዎን እያመጠልዎት መውሰድዎን ያያል። ስለ
ቲቢ መድኃኒትዎ በተመለከተ ማንኛቸውም ጥያቄዎች ወይም ችግሮች ካሉ ለጤና አጠባበቅ ሠራተኛዎ ለመንገር እርግጠኛ ይሁኑ።
 ወደ ሥራ፣ ት/ቤት፣የአምልኮዎ ሥፍራ፣ ቤተ መጻህፍት፣ ወይም ሱቅና የፖስታ ቤት ወደ መሳሰሉ የህዝብ ቦታዎች አይሂዱ።
 አውቶቡሶችን፣ታክሲዎችን፣ ባቡሮችን፣እና አይሮፕላኖችን ጨምሮ የህዝብ ማመላለሻዎችን አይጠቀሙ።
 ወደ ሁሉም የህክምና ቀጠሮችዎ ይሂዱ። ሀኪምዎ ምርመራ አድርግልዎት የቲቢ መድኃኒትዎ መሥራትዎን ያረጋግጣል። በቀጠሮ ካልተገኙ
፣ቲቢዎን ለማዳን ረጅም ጊዜ ሊፈጅ ይችላል።
 ሀኪምዎ ወይም ነርስዎ ልዩ ጭንብል ይሰጥዎታል። ወደ ሆስፒታል ወይም ክሊኒክ በሚሄዱበት ጊዜ ይህን ጭንብል ያድርጉ።
 ሀኪምዎ ወይም የህዝብ ነርስዎ ጭንብልዎን ትተዎ ወደ ዳህና ሥራዎቹዎ እንድመለሱ ዘንድ ይነግሩዎታል።
ስለ ቲቢ ወይም ስለ ህክምናዎ ጥያቄዎች ቢኖሩብዎ ሀኪምዎ ወይም የህዝብ ነርስዎን ያነጋግሩ።  

አሰተያት መስጫ

ተላላፊ የሳንባ ነቀርሳ የተመለከቱ ንባቦች

ሳምታዊ የጤና ትምህርት/Weekly Health Education Post for Community-አራተያ ሳምንት

ድንገተኛ የወሊድ መከላከያ

ድንገተኛ የወሊድ መከላከያ እንክብሎች ከወሊድ መከላከያ ዘዴዎች ዉስጥ የሚመደቡ ሲሆን አገልግሎታቸዉ አንዲት ሴት በድንገት ያለመከላከያ የግብረስጋ ግንኙነት ካደረገች ወይም እየወሰደች ያለዉ የወሊድ መከላከያ ዘዴ እየሰራ ካልሆነ የሚወሰድ ነዉ፡፡
ስለሆነም ይህ የወሊድ መከላከያ አንክብል እንደዋነኛ የወሊድ መከላከያ ዘዴ ሳይሆን እንደመጠባበቂያ ለድንገተኛ ጊዜ ብቻ/ for back-up contraception only/ የሚገለግል ነዉ፡፡ ፐላን ቢ ዋን ስቴፕ የሚባለዉ ድንገተኛ ወሊድ መከላከያ እንክብል ያለሃኪም ትዕዛዝ ሊገዛ የሚችል ነዉ፡፡
ድንገተኛ የወሊድ መከላከያ እንክብል የተረገዘ እርግዝናን አያቋርጥም፡፡ ነገር ግን እንደወሰዱበት የወር አበባ ዑደት ወቅት ከሚከተሉት መንገድ በአንዱ እርግዝና እንዳይፈጠር ሊያደርግ ይችላል፡፡ የእንቁላልን ከአብራኳ አኩርቶ መዉጣትን የመከላከል/የማዘግየት፣የወንድና የሴት የዘር ፍሬዎች እንዳይገናኙ መከላከል አሊያም ቢገናኙም የማህፀን ግድግዳ ላይ እንዳይጣበቁ መከላከል ናቸዉ፡፡
ድንገተኛ የወሊድ መከላከያ እንክብሎች ድንገተኛ የሆነና ያለምንም ጥንቃቄ ከተደረገ የግብረ ስጋ ግንኙነት በኃላ የሚከሰትን እርግዝና የመከላከል ብቃት አላቸዉ፡፡ ነገር ግን ከሌሎቹ የወሊድ መከላከያ ዘዴዎች ጋር ሲነፃፀሩ የመከላከል ብቃታቸዉ ስለሚያንስ በተደጋጋሚና በመደበኛነት መዉሰድ አይመከርም፡፡ እንዲያዉም ድንገተኛ የወሊድ መከላከያ እንክብሎችን በትክክልም ተጠቅመዉ እረግዝናን ሳይከላከሉ ሊቀሩ ይችላሉ፡፡ በተጨማሪም የአባለዘር በሽታዎችን ሊከላከሉ አይችሉም፡፡
ድንገተኛ የወሊድ መከላከያ እንክብሎችን ነፍሰጡር መሆንዎትን ካወቁ እንዳይወስዱ ይመከራሉ፡፡
የድንገተኛ የወሊድ መከላከያ እንክብሎች የጎንዮሽ ጉዳቶች መድሃኒቶቹን ከወሰዱ በኃላ ለተወሰኑ ቀናቶች ሊቀጥሉ የምችል ሲሆን እነርሱም
               • ማቅለሽለሽ/ ማስታወክ
               • መደበት
               • የድካም ስሜት/መደካከም
               • የራስ ምታት
               • የጡት ህመም
               • በወር አበባ ዑደት መካከል ከማህፀን ደም መፍሰስ
               • የታችኛዉ የሆድ ክፍል ላይ ህመም/ቁርጠት መኖር
               • የወር አበባ ዑደትዎን ማዛባት፡- የወር አበባ ዑደትዎ ከሚመጣበት ቀን ተጨማሪ ለአንድ ሳምንት መራዘም፡፡ የወር አበባ

 

ዑደትዎ ድንገተኛ የወሊድ መከላከያ እንክብሉን በወሰዱ በ3ና 4 ሳምንታት ዉስጥ ካልመጣ የእርግዝና ምርመራ ማድረግ ያስፈልጋል/ ይመከራል፡፡
መቼ መወሰድ አለበት፡- የመከላከያ እንክብሉ የመከላከል ብቃቱ ብቁ እንዲሆን የመከላከያ እንክብሉን ግንኙነት ካደረጉ በኃላ ወዲያዉ መዉሰድ፤ ከ72 ሰዓታት ዉስጥ ግን መዉሰድ አለበት፡፡ ድንገተኛ የወሊድ መከላከያ እንክብል በወር አበባ ዑደቱ በየትኛዉም ጊዜ ሊወሰድ ይችላል፡፡

ሳምታዊ የጤና ትምህርት/Weekly Health Education Post for Community-ሦስተያ ሳምንት -Trachoma

ሳምታዊ የጤና ትምህርት/Weekly Health Education Post for Community-ሁለተያ ሳምንት -ጨብጥ/Gonorrhea

News/ዜና

For Third Year(Level-IV) Students

February 03, 2018

Your  Aseptic Compounding final exam will held on thursday and frieday at 8:00 local time in the  afternoon

February 03, 2018

Assigned should avail as per schedule

One five leadres of each sections should collect their form from the department

February 03, 2018

One to five leader should collect their weekly discussion form from the department on monday at 2:00 local time.This form submitted on frieday at 11:00 local time.Leaders should take attendance during discussion time.Any students should avail on frieday in their class room for discussion.

One five leadres of each sections should collect their form from the department

Please reload

bottom of page